የአዲስ አበባ የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል በህገ ወጥነቱ ገፍቷል

ፍኖተ ነፃነት
By ፍኖተ ነፃነት April 3, 2014 06:29

የአዲስ አበባ የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል በህገ ወጥነቱ ገፍቷል

10001397_10201786540326105_1371071297_n

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለከተማው መስተዳድር የሰላማዊ ሰልፍና ማሳወቂያ ክፍል መጋቢት 28 ቀን 2006 የሚያደርገውን ሰላማዊ ሰልፍ የእውቅና ክፍሉ ሰልፉን ማካሄድ አትችሉም በማለት መከልከሉ ህገ ወጥ መሆኑን በመጥቀስ አማራጭ ቦታዎችን የሚያቀርብ ደብዳቤ መጋቢት 19 ቀን 2006 ለማሳወቂያ ክፍሉ በድጋሚ ልኮ ነበር፡፡
መጋቢት 2 ቀን 2006 ለአንድነት የደረሰው ሌላኛው የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ህገ ወጥ ደብዳቤ ፓርቲው በአማራጭነት ያቀረባቸው ቦታዎች የከተማ አስተዳደሩ የስብሰባና የሰላማዊ ሰልፍ አሰራር ስነ ስርዓት አንቀጽ 5.1 መሰረት የተከለከሉ ስፍራዎች በመሆናቸው የተጠየቀውን የሰላማዊ ሰልፍ የእውቅና ጥያቄ ተቀባይነት ያላገኘ መሆኑን እንገልጻለን››ይላል፡፡
የእውቅና ክፍሉ ለአንድነት በጻፈው ደብዳቤ የጠቀሰው ‹‹ስነ ስርዓት›› ለህዝብ ግልጽ ያልተደረገ ፓርቲዎች የማያውቁት ከመሆኑም በላይ በአዋጅ ተለይቶ የተቀመጠውን የሚጣረስ ነው፡፡አንድነት ፓርቲ መስተዳድሩ የጻፈለትን ደብዳቤ እንደመጀመሪያው ህገ ወጥ ሆኖ በማግኘቱ ሰላማዊ ሰልፉን ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማይል አስታውቋል፡፡

ፍኖተ ነፃነት
By ፍኖተ ነፃነት April 3, 2014 06:29