የአቶ አስራት ጣሴ ይግባኝ ለሚያዝያ 1 ተቀጠረ

ፍኖተ ነፃነት
By ፍኖተ ነፃነት April 2, 2014 11:22

12 ገፆችን የያዘው የአቶ አስራት ጣሴ ይግባኝ በሶስት ገፅ አጥሮ እንዲቀርብ ትዛዝ ተሰጠ፡፡ ፍርድ ቤቱ ይህን ትዕዛዝ የሰጠው ትላንት መጋሲት 23 ቀን የአቶ አስራት ጣሴ ጠበቃ አቶ ተማም አባቡልጉ ለልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 11ኛ የፍትሀብሔር ችሎት ያቀረቡት የይግባኝ አቤቱታ ጥልቅና ዝርዝር እንዲሁም በሪሰርች ወረቀት ደረጃ የቀረበ መሆኑን በመጠቆም ነው፡፡ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ የተቃወሙት ጠበቃ ተማም የይግባኝ አቤቱታው ማጠር እንደሌለበት ቢሞግቱም ዳኛው“ አቤቱታውን በሶስት ገፅ አሳጥራችሁ የማታመጡ ከሆነ ይግባኙን ውድቅ አደርገዋለሁ” በማለት ለሚያዚያ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥተዋል፡፡Asrat

ፍኖተ ነፃነት
By ፍኖተ ነፃነት April 2, 2014 11:22