አቶ አስራት ጣሴ ይግባኝ ነገ ይታያል

ፍኖተ ነፃነት
By ፍኖተ ነፃነት March 31, 2014 07:23

አቶ አስራት ጣሴ ይግባኝ ነገ ይታያል

Asrat

አንድነት ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ አስራት ጣሴ በሁለት አመት ገደብ የተላለፈባቸውን የስድስት ወር እስራት በመቃወም ለከፍተኛው ፍርድቤት ስገቡት ይግባኝ ነገ መጋቢት 23 ቀን 2006ዓ.ም እንደሚታይ ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡

አቶአስራት ለፍኖተ ነጻነት እንዳስረዱት በቅርቡ አዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የሰጡትን የግል አስተያየት ተከትሎ የተላለፈባቸውን የስድስት ወር እስራት በመቃወም 11 ገፅ ያለው ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አስገብተዋል፡፡ የአቶ አስራት ይግባኝ አገ በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 11ኛ የፍትሃ ብሔር ችሎትነገ መጋቢት 23 ቀን 2006ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ እንደሚታይ ታውቋል፡፡

አቶ አስራት ባልተከሰሱበት የህግ አንቀፅ በሁለት አመት ገደብ የተላለፈባቸውን የስድስት ወር እስራት እንደተፈረደባቸውና ግልፅ ባልሆነ ምክንያት ለ11 ቀናት መታሰራቸው አይዘነጋም፡፡

ፍኖተ ነፃነት
By ፍኖተ ነፃነት March 31, 2014 07:23