በተቃውሞአቶ መለስ ሃኪም ይረፉ አላቸው፤ህዝቡ ግን “ይረፉ” ካለ ቆይቷል

ፍኖተ ነፃነት
By ፍኖተ ነፃነት July 29, 2012 17:54

በተቃውሞአቶ መለስ ሃኪም ይረፉ አላቸው፤ህዝቡ ግን “ይረፉ” ካለ ቆይቷል

ባለፈው ሳምንት አቶ በረከት ስምኦን መግለጫ
ሰጥተው ነበር። በመግለጫቸውም የጠቅላይ
ሚኒሰትሩን ህመመም በይፋ አምነዋል።
በነገራችን ላይ ጋዜጣዊ መግለጫው እየተሰጠ
ድንገት ወደ አዳራሹ የመግባት እድል ቢያገኙ አቶ
በረከት ስምኦን መሀል ላይ ቁጭ ብለው በግራ
እና በቀኝ ጋዜጠኞች ከበዋቸው፤ ከጀርባቸው
የአቶ መለስ እና የአቶ ግርማ ፎቶ ተሰቅሎ
ሲመለከቱ ሃዘን ቤት የመጡ ነው የሚመስልዎ!
ከሁለቱም ፎቶ ስር የሆነች ብልጭልጭ ነገር
ቢሰቀልማ ፎቶግራፋቸውን እያዩ እንባዎ እርግፍ
እርግፍ ሊል ይችል ነበር። የምር ግን ይሄ ፎቶ
ሰቀላ ለማሟረት እንጂ ለወዳጅነት አይመስልም!
እኔ የምለው አቶ ግርማንስ በቃ ረሳናቸው ማለት

በነገራችን ላይ አቶ ሽመልስ ከማል
ባለፈው ጊዜ ስለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መታመም
ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ “ይሄ
የኢሳት ወሬ ነው!” ብለው ነበር። ያን ግዜ
ብዙ ሰው አልገባውም ነበር። ይሄ የኢሳት ወሬ
ምንድነው? የሚለውን ጥያቄ የአቶ ሽመለስ
አለቆች አቦይ ስብሐት እና አቶ በረከት ስሞንን
መጠየቅ በቂ ነው። እነርሱ እንዳረጋገጡት ታድያ
“የኢሳት ወሬ” ማለት ታማኝ ምንጭ ማለት ሆኖ
እናገኘዋለን።
እኔ የምለው አቶ ሽመልስን ግን መንግስታችን
እንዲህ መጫወቻ ያደረጋቸው በምን ጥፋታቸው
ይሆን!? የሆነ ጊዜ “የአሜሪካን ድምፅን እኛ
አላፈንም ኢህአዴግ እንዲህ አይነት አፈና ማድረግ
ባህሪው አይደለም።” ብለው መግለጫ በሰጡ
በስንተኛው ቀን አቶ መለስ “እሱን ዝም በሉት
የአሜሪካን ድምፅን አፍነናል!” ሲሉ ተናገሩ።
አሁን በቅርቡም “ስካይፕ ይከለከላል የተባለው
ውሸት ነው።” አሉ አቶ በረከት ደግሞ ተነስተው
“እሱ ምን ያውቃል ስካይፕንም ሆነ ሌሎች
የኢንተርኔት ቴክኖሎጂዎችን እንቆጣጠራለን!”
ሲሉ መግለጫቸውን ውድቅ አደረጉባቸው።
ደግመው፤ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ አልታመሙም!”
አሉን ነገሩ ግን ወዲህ ሆነ… በጥቅሉ እርሳቸው
የሚሰጡት መግለጫ ማላገጫ እንዲሆን ስለምን
እንደተፈረደባቸው ግራ ያጋባል!
የሆነ ሆኖ መለስ አሁን ተይዘዋል።
ከወዳጅነታችን የተነሳ “ተይዘዋል” አልን እንጂ

ፍኖተ ነፃነት
By ፍኖተ ነፃነት July 29, 2012 17:54